በዕለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 8:16-28፡ "ወምሴተ ከዊኖ" - "በመሸም፡ጊዜ፡አጋንንት፡ያደረባቸውን፡ብዙዎችን፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ፤በነቢዩ፡በኢሳይያስ፦ርሱ፡ድካማችንን፡ተቀበለ፡ደዌያችንንም፡ተሸከመ፡የተባለው፡ይፈጸም፡ዘንድ፥መናፍስትን፡በቃሉ፡አወጣ፥ የታመሙትንም፡ዅሉ፡ፈወሰ።ኢየሱስም፡ብዙ፡ሰዎች፡ሲከቡት፡አይቶ፡ወደ፡ማዶ፡እንዲሻገሩ፡አዘዘ። አንድ፡ጻፊም፡ቀርቦ፦መምህር፡ሆይ፥ ወደምትኼድበት፡ዅሉ፡እከተልኻለኹ፡አለው። ኢየሱስም፦ለቀበሮዎች፡ጕድጓድ፡ለሰማይም፡ወፎች፡መሳፈሪያ፡አላቸው፥ለሰው፡ልጅ፡ግን፡ራሱን፡የሚያስጠጋበት፡የለውም፡አለው። ከደቀ፡መዛሙርቱም፡ሌላው፦ጌታ፡ሆይ፥አስቀድሜ፡እንድኼድ፡አባቴን፡እንድቀብር፡ፍቀድልኝ፡አለው። ኢየሱስም፦ ተከተለኝ፥ ሙታናቸውንም፡እንዲቀብሩ፡ሙታንን፡ተዋቸው፡አለው። ወደ፡ታንኳም፡ሲገባ፡ደቀ፡መዛሙርቱ፡ተከተሉት። እንሆም፥ማዕበሉ፡ታንኳዪቱን፡እስኪደፍናት፡ድረስ፡በባሕር፡ታላቅ፡መናወጥ፡ኾነ፤ርሱ፡ግን፡ተኝቶ፡ነበር። ደቀ፡መዛሙርቱም፡ቀርበው፦ጌታ፡ሆይ፥አድነን፥ጠፋን፡እያሉ፡አስነሡት። ርሱም፦ እናንተ፡እምነት፡የጎደላችኹ፥ስለ፡ምን፡ትፈራላችኹ፧ አላቸው፤ከዚህ፡በዃላ፡ተነሥቶ፡ ነፋሱንና፡ባሕሩን፡ገሠጸ፥ታላቅ፡ጸጥታም፡ኾነ። ሰዎቹም፦ነፋሳትና፡ባሕርስ፡ስንኳ፡የሚታዘዙለት፥ ይህ፡እንዴት፡ያለ፡ሰው፡ነው፧እያሉ፡ተደነቁ። ወደ፡ማዶም፡ወደ፡ጌርጋሴኖን፡አገር፡በመጣ፡ጊዜ፥አጋንንት፡ያደሩባቸው፡ኹለት፡ሰዎች፡ከመቃብር፡ወጥተው፡ተገናኙት፤ እነርሱም፡ሰው፡በዚያ፡መንገድ፡ማለፍ፡እስኪሳነው፡ድረስ፡እጅግ፡ክፉዎች፡ነበሩ።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨








