
የማሊ መከላከያ ሚኒስትር ጄኔራል ሳዲዮ ካማራ በአገር አቀፍ ደረጃ በወታደራዊ ጣቢያዎች ላይ በተደረጉ የተቀናጁ ጥቃቶች መገደላቸውን የመንግስት ቃል አቀባይ አረጋግጠዋል። ካማራ የተገደሉት ጥቃት አድራሾቹ በመኖሪያ ቤታቸው ላይ ባነጣጠሩት ጥቃት መሆኑን ቃል አቀባዩ ኢሳ ኦስማን ኩሊባሊ እሁድ እለት በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
በካቲ ጋሪሰን ከተማ የሚገኘው የካማራ መኖርያ ቤት ቅዳሜ እለት በአልቃይዳ ተባባሪ በሆነው የቱዋሬግ አማፂ ቡድን ጥቃት ተከፍቶበታል። ካማራ እ.ኤ.አ. በ2020 እና በ2021 ከተደረጉ መፈንቅለ መንግስት በኋላ ስልጣኑን ለተቆጣጠረው ወታደራዊ መንግስት ማዕከላዊ ሰው ነበሩ።
በገዥው ወታደራዊ አመራር ውስጥ በጣም ተደማጭነት ካላቸው ሰዎች አንዱ የነበሩ ሲሆን አንዳንዶች ወደፊት የማሊ መሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ይናገሩ ነበር። የካማራ ህልፈት ለሀገሪቱ ታጣቂ ሃይሎች ትልቅ ጉዳት ሆኗል።ታጣቂዎች በጊዜያዊው ፕሬዝዳንት አሲሚ ጎይታ ከሚኖሩበት ከዋና ከተማይቱ ባማኮ በስተሰሜን ምዕራብ 15 ኪሜ ርቀት ላይ በምትገኘው ካቲ የካማራ መኖሪያ ቤት ላይ የአጥፍቶ ጠፊ በመኪና ላይ የተጠመደ ቦምብ ጥቃት ፈጽመዋል።
በስምኦን ደረጄ


![مجله خبری تلگرام [ T N M ] Telegram channel](https://cdn.tgdio.com/channels/2026/04/TelNews_Magazine.webp)





![[ ترول تایمز ] Telegram channel](https://cdn.tgdio.com/channels/2026/04/TrollTimes.webp)
