የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት-Holy Trinity University PR Telegram channel photo

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት-Holy Trinity University PR

@holytrinityprPublic Channel

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት-Holy Trinity University PR shares اخبار کسب‌وکار updates and media on Telegram. Join to stay updated.

423

Last views

۲.۴k (2,376 subscribers)
عضو
—
Rating
34
Total Posts
Oct 18, 2026, 2:03 AM
به‌روزرسانی شده
May 13, 2026
Created
Stats

شما در حال مشاهده محتوای فارسی هستید. برای مشاهده محتوا به زبان‌های دیگر، زبان سایت را تغییر دهید.

Channel Information

Channel Information
Channel Nameየቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት-Holy Trinity University PR
Username@holytrinitypr
Categoryاخبار کسب‌وکار
Languageفارسی
Countryایران
عضو2,376
Channel TypePublic Channel
Created۲۳ اردیبهشت ۱۴۰۵
Last Updated۲۶ مهر ۱۴۰۵ • ۴ روز پیش
StatusActive

رتبه‌بندی

رتبه‌بندی جهانی
#36286+109
رتبه‌بندی زبان
#3565+11
رتبه‌بندی دسته‌بندی
#680+4

رشد مشترکان

مجموع: 2.4K30 Days growth: +1989.1%
09/1809/2309/2810/0310/0810/1310/17
رشد مشترکان - 30 Days
DateSubscribers
18:09:20262,178
19:09:20262,178
20:09:20262,251
21:09:20262,251
22:09:20262,251
23:09:20262,251
24:09:20262,251
25:09:20262,251
26:09:20262,251
27:09:20262,251
28:09:20262,251
29:09:20262,251
30:09:20262,251
01:10:20262,251
02:10:20262,251
03:10:20262,251
04:10:20262,251
05:10:20262,251
06:10:20262,251
07:10:20262,251
08:10:20262,251
09:10:20262,251
10:10:20262,251
11:10:20262,251
12:10:20262,251
13:10:20262,251
14:10:20262,251
15:10:20262,251
16:10:20262,251
17:10:20262,376
رشد مشترکان - Weekly
DateSubscribers
Week of 11:05:20262,019
Week of 18:05:20262,019
Week of 25:05:20262,019
Week of 01:06:20262,019
Week of 08:06:20262,019
Week of 15:06:20262,019
Week of 22:06:20262,019
Week of 29:06:20262,019
Week of 06:07:20262,052
Week of 13:07:20262,052
Week of 20:07:20262,052
Week of 27:07:20262,052
Week of 03:08:20262,052
Week of 10:08:20262,052
Week of 17:08:20262,110
Week of 24:08:20262,110
Week of 31:08:20262,140
Week of 07:09:20262,178
Week of 14:09:20262,251
Week of 21:09:20262,251
Week of 28:09:20262,251
Week of 05:10:20262,251
Week of 12:10:20262,376
رشد مشترکان - Monthly
DateSubscribers
May 20262,019
June 20262,019
July 20262,052
August 20262,110
September 20262,251
October 20262,376
رشد مشترکان - Yearly
DateSubscribers
20262,376

آخرین پست‌ها

የሩሲያ እና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት የጋራ ኮሚሽን 4ኛ ጉባኤውን በሞስኮ አካሄደ 

(ቅ.ሥ.ዩ. ጥቅምት 9፣ 2019 ዓ.ም) 

በሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መካከል ያለው የጋራ ኮሚሽን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በሩሲያ መዲና ሞስኮ አካሂዷል። ይህ ከፍተኛ የሁለትዮሽ የምክክር ጉባኤ የተካሄደው የሞስኮ እና የመላው ሩሲያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኪሪል እንዲሁም የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሰጡት አባታዊ ቡራኬ እና መመሪያ መሆኑ ተገልጿል። በአብያተ ክርስቲያናት ቅዱሳን አባቶች ቡራኬ የተወከሉት የሁለቱም ወገን ልዑካን በወንድማማችነት እና በጋራ የትብብር መንፈስ የሁለትዮሽ ውይይቱን በስኬት አከናውነዋል።

በጉባኤው ላይ የሞስኮ ፓትርያርክን በመወከል የሴርጊየቭ ፖሳድ እና ዲሚትሮቭ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኪሪል የሁለትዮሽ ጉባኤውን በጥምር ሰብሳቢነት የመሩት ሲሆን፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በመወከል ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር፣ ተ/ፕ/ር) የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት፣ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሰብሳቢነት ልኡካኑን መርተዋል። በሩሲያ ቤተ ክርስቲያን በኩል የክርስቲያኖች አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ግንኙነት ጸሓፊ የሆኑት አባ እስጢፋኖስ፣ የማርታ እና ማርያም ገዳም እመ ምኔት እማሆይ ኤልሳቤጥ (ፖዝድንያኮቫ)፣ የአብያተ ክርስቲያናት እና ሚዲያ ግንኙነት መምሪያ ምክትል ኃላፊ ቫክታንግ ኪፕሺዜ እና ሰርጌይ አልፌሮቭ የተሳተፉ ሲሆን፤ የሞስኮ ፓትርያርክ ምክትል ቻንስለር ብፁዕ አቡነ ሲልዋን በእንግድነት ተገኝተዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በኩል ደግሞ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ እንዲኹም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በመንበረ ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስ ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ቀሲስ ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል በጉባኤው ላይ ተሳትፈዋል።

ተሳታፊዎቹ በ3ኛው ጉባኤ ወቅት የተያዙ ዕቅዶችን አፈጻጸም የገመገሙ ሲሆን በጉባኤው ማጠቃለያ ላይም የሁለቱን አብያተ ክርስቲያናት ታሪካዊና ዘላቂ ግንኙነት የሚያጸና የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። በውይይቱም ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሱ ጫናዎችን የመከላከል ጉዳይ ዋና ትኲረት ተሰጥቶታል፡፡ በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዩክሬን እና በምሥራቅ አውሮፓ በሚገኙ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምዕመናን ላይ የሚደረገውን ስደት የምትቃወም መሆኗን ገልጻለች። በተመሳሳይ መልኩ የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች ጥቃት ለሚደርስባቸው የተዋሕዶ ምዕመናን ያላትን ጥብቅ ድጋፍ ያረጋገጠች ሲሆን ሁለቱም አብያተ ክርስቲያናት ሃይማኖት ለፖለቲካ ጥቅም መዋሉን አጥብቀው ኮንነዋል።

በሌላ በኩል ሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት በትምህርት፣ በሚዲያ፣ በቤተ ክርስቲያን ሥነ ጥበባት እና በሰብኣዊ አገልግሎት ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ለማስፋፋት ተስማምተዋል። በዚህም መሠረት የሞስኮ ነገረ መለኮት ትምህርት ቤት የኢትዮጵያ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጁነቱን ያረጋገጠ ሲሆን በሦስተኛ (በዶክትሬት) ዲግሪ መርሐ ግብራት፣ በትምህርት ጽሑፍ ህትመቶች እና በኢትዮጵያ ጥናቶች ዙሪያ ከሩሲያ ሳይንስ አካዳሚ ጋር በጋራ ለመሥራት ከስምምነት ተደርሷል። ከዚህ በተጨማሪ በሞስኮ በሚገኘው የቅዱስ አሌክሲስ ማዕከላዊ ሆስፒታል፣ በአዲስ አበባ በሚገኘው ምግባረ ሠናይ ሆስፒታል እና በደጃዝማች ባልቻ የሩሲያ ቀይ መስቀል ሆስፒታል መካከል የማኅበራዊ እና የሕክምና አገልግሎት ትብብር የሚያደረግ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት የሚገኙ ቅዱሳት መካናትን የሚያስተሳስሩ መንፈሳዊ ጉዞዎችን እንደገና ለማስጀመር እና በገዳማውያን መካከልም የጋራ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ መወሰኑ ተገልጿል።

የዚህ የ4ኛው ጉባኤ ውሳኔዎች እና የመጨረሻ ስምምነቶች ለሁለቱ አብያተ ክርስቲያናት ቅውዱሳን ፓትርያርኮች እና ቅዱሳን ሲኖዶሶች ለምክክርና ለውሳኔ የሚቀርቡ ሲሆን፤ ኮሚሽኑ 5ኛ መደበኛ ጉባኤውን በ2028 (እ.አ.አ.) በኢትዮጵያ ለማካሄድ ወስኖ ስብሰባውን አጠናቅቋል።

የዜናው ምንጭ፡- https://mospat.ru/en/news/94560/
405004
እረኝነት፣ ስብከተ ወንጌልና ድኅነተ ነፍሳት

(ቅ.ሥ.ዩ ጥቅምት 6 ቀን 2019 ዓ.ም)
የቤተ ክርስቲያን እውነተኛ ሀብት በገንዘብና በቁሳዊ ንብረት ብቻ ሳይሆን፣ በወንጌል ወደ ክርስትና በሚመለሱና በእምነታቸው በሚጸኑ ሕዝበ ክርስቲያኖች ሕይወት ይገለጣል። የአንድ ሊቀ ጳጳስ የእረኝነትና ስብከተ ወንጌል ኃላፊነትም በተመደበበት ሀገረ ስብከት (ሕዝበ ክርስቲያን) በመንፈሳዊ እንክብካቤ፣ በማስተማር፣ በመምራትና የወንጌልን ብርሃን ወዳልደረሰባቸው አካባቢዎች ማድረስ መሆኑ ይታወቃል።

በ45ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ላይ የቀረበው ሪፖርት በደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፋት በተከናወነው “ዘመቻ ፊልጶስ” የተመዘገበውን ውጤት፤ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) ለሚመሩት ሕዝብ ያላቸውን የእረኝነት ኃላፊነት የሚያሳይ ነው።


የእረኝነት ስኬት የሚለካው በስብከተ ወንጌል በሚመለሱ ነፍሳት ብዛትና በሚጸኑበት የእምነት ሕይወት ዋነኛው መሆኑን የሚያሳየን በደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት
በ180 የስብከተ ወንጌል ጉባኤያት 23,199 አላማኝ ሕዝብ ወደ ቅድስት ቤተክርስቲያን መመለሳቸው አይነተኛ ምስክራችን ነው።
------------

“ዘመቻ ፊልጶስ” በሚል ስያሜ በደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት በተካሄዱ 180 የወንጌል ጉባኤያት 23,199 አሕዛብ ወደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት መመለሳቸው ተገለጸ።

ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር)፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንትና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ወንጌል በአካባቢው እንዲስፋፋና ለሕዝቡ የበለጠ ተደራሽ እንዲሆን ባላቸው ፍላጎት መሠረት፣ “ዘመቻ ፊልጶስ” በሚል ርዕስ ስብከተ ወንጌልን ለማጠናከር የተቀናጁ ሐዋርያዊ እንቅስቃሴዎች ተከናውነዋል።

በዚህ ሐዋርያዊ እንቅስቃሴ በተለይም ዓቢይ ጾምን ምክንያት በማድረግ፣ የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች፣ የአብያተ ክርስቲያናት አስተዳዳሪዎች: ሰባክያን ወንጌል: መንፈሳዊያን ማኅበራትና ሰ/ትምህርት ቤቶች በቅንጅት በመሥራት በተለያዩ አካባቢዎች 180 የስብከተ ወንጌል ጉባኤያትን አካሂደዋል። በእነዚህ ጉባኤያት በተደረገው የሰብከተ ወንጌል አገልግሎት፣ ከተለያየ የእምነት ሕይወት 23,199 ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መመለሳቸው ተገልጿል።

የዘመቻው አንዱ ዋና መለያ በሁለት ጽዋዎች (ዋንጫዎች) አማካይነት ስብከተ ወንጌልን ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ማድረስ ነበር። የመጀመሪያውን ጽዋ (ዋንጫ) በጂንካ ከተማ በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት በማዘዋወር ልዩ ሐዋርያዊ አገልግሎት ተከናውኖበታል። ሁለተኛው ጽዋ (ዋንጫ) ደግሞ በወረዳዎችና የወንጌል ጉባኤ አይተው የማያውቁ የገጠር ከተሞች ድረስ በመድረስ ሰፊ የስብከተ ወንጌል ንቅናቄ እንዲፈጠር አስችሏል።

ይህ ውጤት የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ለማካሄድ የተደረገውን ጥረት የሚያሳይ ሲሆን፣ በተለይም ወንጌል በብዛት ወዳልደረሰባቸው አካባቢዎች ሐዋርያዊ አገልግሎት መድረሱን ያመለክታል። የሀገረ ስብከቱ አገልጋዮች በጋራ ያከናወኑት ይህ ተግባር የወንጌልን መልእክት ለማስፋፋትና በአካባቢው የመንፈሳዊ ሕይወት እድገትን ለማጠናከር ያለውን ትልቅ ትርጉም ያሳያል።

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መላው ማኅበረ ሰብም በዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚደንትና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) በሀገረ ስብከታቸው ባስመዘገቡት ሐዋርያዊ ተልዕኮ ውጤት የተሰማውን ደስታ ይገልጻል።
3,800001
በብፁዕ ዶ/ር አቡነ ፊልጶስ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) መሪነት ለቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የሥልጠናና የምክክር ጉባኤ ተካሔደ
___
(ቅ.ሥ.ዩ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም)
በብፁዕ ዶ/ር አቡነ ፊልጶስ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት፣ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መሪነት፣ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን በማስመልከት ለዩኒቨርሲቲው መምህራን የተዘጋጀ የአንድ ቀን ሥልጠናና ምክክር ጉባኤ ዛሬ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ።

መርሐ ግብሩ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ፊልጶስ Educational Eco System in E.O.T.C በሚል ርእስ ሥልጠና የሰጡ ሲሆን ብፁዕነታቸው በመማር ማስተማር ሂደት፣ መምህራኑ ሊኖራቸው በሚገቧቸው ኃላፊነቶችና ተማሪዎችን በማገልገል ዙሪያ ለመምህራኑ ሰፊ ሥልጠናና መመሪያ ሰጥተዋል።

ከሰዓት በኋላ በቀጠለው የመምህራን ጉባኤ ብፁዕነታቸው ሥልጠና በሰጡበት ርእሰ ጉዳይ መነሻነት መምህራኑ በስምንት ቡድኖች ተከፋፍለው በተለያዩ የውይይት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በጋራ የተወያዩ ሲሆን፣ ከውይይቱ በኋላም እያንዳንዱ ቡድን የደረሰበትን ሐሳብና የውይይቱን ውጤት ለተሳታፊዎች አቅርበው ተወያይተውበታል።

ስምንቱ ቡድኖችም በቤተ ክርስቲያኒቱ ታላላቅ አባቶች ስም ሰይመው የአንድ ሙሉ ቀን ወርክሾፕ መምህራኑ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በተሻለ መንፈስና በጋራ ትብብር እንዲወጡ የሚያግዝ የምክክርና የልምድ ልውውጥ መድክ ላይ በንቃት ተሳትፈዋል።

ብፁዕነታቸው ከውይይቱ የተገኙ ግብአቶችን መነሻ አድርገው ለመማር ማስተማሩ አጋዥ የሚኾኑ ግብአቶችን አክለው በቅርብ ቀን ቀጣይ ውይይት እንደሚደረግ ቃል ገብተውዋል።

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት
1,560000
Video
በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምዕመናን በሙሉ!


በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ በ2018 ዓ.ም በርቀት እና በኦንላይን ዘርፍ በዲግሪ መርሐ ግብር የነገረ መለኮት ትምህርትን ለማስተማር ከነሐሴ  20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የአዲስ ተማሪዎችን ምዝገባ እያካሄደ ይገኛል፡፡


ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ በዩኒቨርስቲው የርቀት እና በይነ መረብ ኮሌጅ በአካል ወይም በወኪል በመቅረብ ዋናውን የትምህርት ማስረጃችሁንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በማቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡


ማሳሰቢያ፡ ሁሉም አመልካቾች ከሚኖሩበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲን የሰበካ አባልነት የድጋፍ ደብዳቤ እና 4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251949000333 እና +251949000777 ይደውሉ፡፡

በቴሌግራም ቻናላችን @HTUCODEE ይከታተሉን
2,440007
“ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ (ኤፌ. 5፡16)።

ዕድሜ ለንስሓ እየሰጠ፤ አገልግሎታችንን እየባረከ፤ በአባትነት ፍቅሩ ከዘመን ወደ ዘመን የሚያሸጋግረን ልዑል እግዚአብሔር እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ማርቆስ 2018 ዓ.ም ወደ ዘመነ ቅዱስ ሉቃስ 2019 ዓ. ም በሰላም አሸጋግራችሁ።

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በስብከተ ቃሉ ላመኑ፣ በሞተ እስጢፋኖስ በዓለም ሁሉ ለተበተኑ ምእመናን በላከላቸው መልእክት ውስጥ ያለፉበትን የኃጢአት ዘመን ትተው፣ በንስሓ ታጥበው፣ ዘመኑን እየተመለከቱ በማስተዋል በሃይማኖት እንዲኖሩ የጻፈላቸው የሕይወት ቃል ነው።

የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ልጆች! ዘመን ተለውጦ አዲስ ዘመን ሲተካ ለንስሓ አዲስ ጊዜ እየተሰጠን መኾኑን መዘንጋት የለብንም። እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጅ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ “ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ (ኤፌ. 5፡16) እንድል ቅዱስ መጽሐፍ በዚህ ከፉ ዘመን ራስን በመግዛትና በመቆጣጠር ቸግርን መጋፈጥና ማለፍ የክርስትና ግደታችን መሆኑን መዘንጋት የለብንም።

​የሰው ልጅ ያለፈ ሕይወቱን እየገመገመ፣ መተው ያለበትን እየተወ፣ ከስሕተቱ ተምሮ ንስሓ እየገባ፣ በምክረ ካህን ራሱን እየለወጠ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ነገር ፈትኖ እየመረጠ ክርስቲያናዊ ሥርዓትን ጠብቆ እንዲኖር በእግዚአብሔር ታዝዟል።

ነቢዩ ዳንኤል “ጥበብና ኃይል ለእርሱ ነውና የእግዚአብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይባረክ፤ ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል” (ዳን 2፥20) በማለት እግዚአብሔር በጥበቡ ጊዜያትንና ዘመናትን እንደሚለውጥ ነግሮናል። አምላካችን በጥበቡ ዘመንን ሲለውጥ የሰው ልጅም ከቆመበት ሥፍራ እግዚአብሔርን ደስ ወደሚያሰኝ ተግባር እንዲቀርብና በተሰጠው ዘመን ሰውንም እግዚአብሔርንም እንዲያገለግል እንጂ የዚህ ዓለም ምርኮኛ እንዲሆን አይደለም።

​በመጽሐፍ እንደተነገረን የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙት ነገሮች ማለትም ፍቅርን፣ በጎነትን፣ የዋሕነትን፣ ከኃጢአት ርቆ በንስሐ ጸንቶ መኖርንና በጥበብ መመላለስን የማንነቱ መገለጫ ያደርግ ዘንድ ነው። በአዲሱ ዓመትም በልባችን መታደስ ተለውጠን ከኃጢአት ርቀን በንስሐ ጸንተን ሕገ እግዚአብሔርን እየጠበቅን ዘመኑን መስለን ሳይሆን ዘመኑን ዋጅተን የእግዚአብሔር መንግሥት ወራሾች ለመሆን መዘጋጀት ይኖርብናል።

​የተወደዳችሁ በሩቅም በቅርብም የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያዊያት “በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ”(ኤፌ 4፥3) ብሎ እንደተናገረው በአዲሱ ዓመት አሮጌውን የመለያየት የዘረኝነት፣ የምንደኝነት፣ የጸብ፣ የመወሻሸት፣ የመገፋፋት፣ የመጠፋፋት፣ ወዘተ... አመል ፀባያችንንና ልምዳችንን በማስወገድ ለአንድነት፣ ለፍቅር ለሰላም፣ ለይቅርታ፣ ለእውነት፣ ለበረከት የተዘጋጀን የክርስቶስ መለእክተኞች መሆን እንደሚገባን በአጽናዖት ለማሳሰብ እወዳለሁ። አዲሱ ዓመት የንስሓ፣ የይቅርታ፣ የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅር ይሁንልን!

አባ ፊልጶስ
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት፤
የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
መስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም
11,200007
“መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ"
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሓዱ አምላክ፣ አሜን !

በሀገር ውስጥና በመላው ዓለም የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታዮች በሙሉ!

የሰውን ወገን ለማዳን የልጁ ማደሪያ ትሆን ዘንድ ድንግል ማርያምን የመረጠ መፍቀሬ ሰብእ እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ዓሥራ ስምንት ዓመተ ምሕረት ጾመ ማርያም ኣደረሰን ኣደረሳችሁ!
“ወእመሰ ታፈቅሩኒ ዕቀቡ ትእዛዝየ፡- ከወደዳችሁኝስ ትእዛዜን ጠብቁ" (ዮሐ.14፥15)፤
ፍቅር የሕያዋን ኣካላት ረቂቅ መገናኛ ነው፣ ሕያዋን ኣካላት በውጫዊው ግዙፍ ኣካላቸው በተወሰኑ ጊዜያትና ቦታ ይገናኛሉ ፤ ስለ ጋራ ጉዳያቸውም በጋራ ይመክራሉ፤ ይበልጥም ይቀራረባሉ፡፡

ይሁንና የሕያዋን ኣካላት ግንኙነት በኣካል በጊዜና በቦታ ብቻ የተወሰነ ኣይደለም፣ በፍቅረ መንፈስ ተገናኝተውም ይግባባሉ፣ ከኣካላዊ ግንኙነት በላይ የበለጠም ይኸው ፍቅረ መንፈስ ነው፤ ከዚህ ኣንጻር እግዚአብሔርንም ማግኘት የምንችለው በዚሁ ፍቅረ መንፈስ ሆነን በእምነት ዓይን ነው!

ይህም በመሆኑ ሓዋርያው ቅዱስ ዮሓንስ በመልእክቱ “በፍቅር የሚኖር በእግዚአብሔርይኖራል፣ እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል" በማለት ያስተምረናል፣ (1ዮሐ. 4፥16) ይህም ማለት ከሱ ጋር በፍቅር ስንገናኝ፤ እሱም በኛ፣ እኛም በእሱ የመኖሩ ኩነት ይፈጠራል ማለት ነው፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

ጌታችን “አፍቅሮ ለእግዚአብሔር ኣምላክከ፤- አምላክህን እግዚአብሔርን ውደደው" በማለት በፍጹም ልባችን እንድንወደው፣ እንደዚሁም ራሳችንን በምንወድበት መጠን እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ ማዘዙን እናውቃለን፤

የመውደዳችን መለኪያ ሚዛንና መገለጫ ምልክትም ትእዛዙን ማክበርና መጠበቅ እንደሆነ “ብትወዱኝስ ትእዛዜን ጠብቁ” በማለት ኣስተምሮናል
ከዚህ ኣኳያ ጌታን መውደድ ማለት ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ግዙፍ ነገር እንጂ ምናባዊና የማይታይ ድብብቆሽ ነገር ኣይደለም ማለት ነው፣

ጌታችንን የመውደድ ነገር ትእዛዙን በመጠበቅ የሚገለጽ ከሆነ ትእዛዙ ምንድን ነው? የሚለውን ማየት ኣስፈላጊ ይሆናል፤ ትእዛዙን በጥቅል ስናይ እግዚአብሔርንና ባልንጀራን በመውደድ እንደሚጠቃለል ራሱ ጌታችን ኣስገንዝቦናል፣

በተለይም በባልንጀራችን ላይ የምንከተለው መውደድ ከላይ እንደተገለጸው “እንደራስህ ኣድርገህ ውደድ" ተብለ በግልጽ ተቀምጦኣል፤
የሰው ባልንጀራ እነማን ናቸው? በሕይወት ያሉት ናቸው? ወይስ የሞቱት? ወገን ዘመድ? ወይስ የሰው ወገን በሙሉ የሚለውንም ማወቅ ኣስፈላጊ ነው፡፡

ጌታችን ነገሩን በዚህ ደረጃ ለያይቶ ኣላስቀመጠም፣ ለምን? ቢባል ባልንጀራ ማለት የተወሰነን የማኅበረ ሰብ ወገን የሚያሳይ ሳይሆን መላውን የሰው ወገን የሚገልጽ በመሆኑ፤ እንደዚሁም የሞቱም ሆኑ ያለነው ሁላችን በእሱ ፊት ሕያዋንና እርስ በእርሳችን ባልንጀሮች በመሆናችን ነው፤

በመሆኑም መዋደዳችንም ሆነ መከባበራችን በሕይወተ ሥጋ ሳለን ብቻ ሳይሆን ከዚያም በኋላ እስከ በሌለው ዕድሜ በመሆኑ ጌታችን በጊዜ በቦታና በከፊል ለይቶ ኣላስቀመጠም፡፡

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት !

ከነሐሴ ፩ ቀን ጀምሮ ለ፲፭ ቀናት የምንጾመው የጾመ ማርያም መነሻ ምክንያቱ የእግዚአብሔርትእዛዝና ፍቅር ነው፣

እግዚአብሔር ሰውን በኣጠቃላይ በተለይም ደግሞ እንደፈቃዱ የኖሩ ቅዱሳንን እንድናከብርኣዞናል ክቅዱሳን ፍጥረታት መካክል ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም የመጀመሪያውን ደረጃ ትይዛለች፤

ይህም በመሆኑ ከፍጥረት ወገን ከሏ ክብር የሚደርስ ባለመኖሩ ከሁሉም ኣብልጠን እናክብራታለን፤

ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዚህ ደረጃ የድንግል ማርያምን ክብር ስትገልጽ ክእግዚአብሔርና ለባስያነ እግዚአብሔር ክሆኑ ቀደምት ኣበው ተምራ ነው!

በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበረው ዕውቁ ቅዱስና ዓለም ዓቀፋዊው አባት ቅዱስ ኤፍሬም የድንግል ማርያምን ክብር! ቅድስና እና ልዕልና ሲናገር “ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፡ ወትፈደፍድ እምሱራፌል፣ እስመ ኮነት ታቦተ ለአሓዱ ዘእምቅድስት ሥላሴ- እሷ ከኪሩቤል ትበልጣለች! ከሱራፌልም ትልቃለች፣ ከቅድስት ሥላሴ ኣንዱ ለሆነው ታቦት ወይም ማደሪያ ሆናለችና" በማለት አስተምሮናል፡፡

በመሆኑም ለስሟ መታሰቢያ በሆነው በዚህ ጾም ድንግል ማርያምን በዚህ ደረጃ ስናክብርትእዛዙን እንጠብቃለን፤ ትእዛዙን በመጠበቃችን ደግሞ እሱን መውደዳችንን እናረጋግጣለን ! እኛ ድንግል ማርያምን እንድንወዳት "እናታችሁ'' ብሎ እንዳዘዘ፣ እሷም ልትወደን “ልጆችዅ ተብላ ታዛለችና ስለኛ ትጸልያለች፡፡

በጸሎቷም ከመከራ ትታደገናለች፤ በኣጠቃላይ በእግዚአብሔር' በቅዱሳንና በእኛ መካከል ያለው ግንኙነት በዚህ ትእዛዝና ፍቅር በትዕይንተ ዓለም ባለች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተሳሰረ ነው፡፡

ስለሆነም በዚህ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም ሱባዔ የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሎትን በማስታረቅ፤ የታመሙትንና የታስሩትን በመጠየቅ፤ ቅዱስ ቍርባንን በመቀበልና ለኃጢኣታችን የንሥሐ ሥርየትን በመለመን ሱባዔውን ልናሳልፍ ይገባል፡፡

በመጨረሻም

በሀገራችንም ሆነ በዓለም ዙሪያ ከባድ ስጋት የሆነው የፍጥረት ኣውዳሚ ጦርነትን በመለኮታዊ ጥበቡና ሥልጣኑ እንዲያስቆምልን በቅን ልቡና፤ በትሑት ሰብእና ሆነን እግዚአብሔርን በዚህ ሱባዔ እንድንጠይቀው ኣደራ ጭምር ኣባታዊ መልክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤

የተባረከና የተቀደስ ጾም ያድርግልን፤

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፣ አሜን!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእስ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘኣኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ነሐሴ 1 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ፤ ኢትዮጵያ
1,470007
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ወቅታዊ ጉዳዮች በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።

ሓምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት እንደሚከተለው ነው፦

መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

"ገባሬ ሣህል እግዚአብሔር፥ ወይፈትህ ለኩሉ ግፉዓን፦
እግዚአብሔር ይቅርታ አድራጊ ነው፤ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።"
(መዝሙር ፻፪፥፮)

ከሁሉ በማስቀደም በሀገር ውስጥ እና በመላው ዓለም የምትኖሩ ኦርቶዶክሳውያን የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንን ሐምሌ 19 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በከፍተኛ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ለሚከበረው፤ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኮ በእምነታቸው የጸኑትን ቅዱስ ቂርቆስንና ቅድስት ኢየሉጣን በመከራቸው መካከል እየተራዳ የእሳቱን ነበልባል እንደክረምት ውኃ ላቀዘቀዘበት፤ በእግዚአብሔር ቃል ኪዳን የታመኑትንም እስከ ሰማዕትነት ፍጻሜ ድረስ የሚያጸና መሆኑን ለምንዘክርበት ታላቅ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እንወዳለን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከዘመነ ሐዋርያት ጀምሮ የወንጌልን ብርሃን በማብራት፣ የሰላምን መንገድ በማስተማር፣ ፍትሕን በማጽናት፣ የተጨነቁትንም በማጽናናት፣ ሕዝብንና ሀገርን እየደገፈች የኖረች ናት።

በዚህ ቅዱስ ተልእኮ ውስጥም መናንያን መነኮሳት እና መነኮሳይያት ዓለምንና ከዓለም የሚገኘውን ጊዜያዊ ክብር፣ ጥቅም፣ ምቾትና የመሳሰሉትን በፈቃዳቸው ትተው፤ በየገዳማቱ በበአታቸው በጾም፣ በጸሎት ተወስነው፤ ሕይወታቸውን በትሕትና ለእግዚአብሔር በመስጠት፤ ስለ ራሳቸው ብቻ ሳይሆን ስለ ሀገር፣ ስለ ሕዝብ፣ ስለ ሰላምና ስለ ዓለም ደኅንነት በመዓልትና በሌሊት የሚጸልዩ የምድራችን በረከቶች ናቸው።

መስቀልን በተሸከሙ፣ ጸሎትን መከታ ባደረጉ፣ ለፍጥረት ሁሉ ምሕረትን በሚለምኑ፣ ራሳቸውን ለመከላከልም ምንም ዓይነት ቁሳዊ ዝግጅት በሌላቸው በእነዚህ መናንያን ላይ እጅን ማንሣት በእግዚአብሔር ዘንድ የተከለከለ፣ በታሪክ ፊትም የሚያሳፍር ድርጊት ነው።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!

በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በቦረና ወረዳ በግዮን አባይ ገዳመ አስቄጥስ ቅድስት አርሴማ፣ አቡነ አረጋዊና ቅዱስ ቂርቆስ የአባቶችና የእናቶች አንድነት ገዳም ሐምሌ 15 ቀን 2018 ዓመተ ምሕረት በተፈጸመው ጥቃት የመናንያን መነኮሳይያት ሕይወት በግፍ መጥፋቱን፤ በርካቶች መቁሰላቸውን፤ በገዳሙና በንዋየ ቅድሳቱ ውድመት መድረሱን ከሀገረ ስብከቱ መግለጫ በከፍተኛ ሐዘን የሰማን ሲሆን፤ በተመሳሳይም በዚሁ ዕለት በሀድያና ስልጤ ሀገረ ስብከት የአምልኮ ሥፍራ በኃይል መፍረሱና በምእመናን ላይ ጥቃት መድረሱ የሚያሳዝንና በፍጹም ተቀባይነት የሌለው የተወገዘ ተግባር ነው።

በመሆኑም የጸሎት፣ የትምህርት፣ የሰላምና የመንፈሳዊ እሴት ማዕከል የሆኑትን ገዳማት መጠበቅ የአንድ ሃይማኖት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ የሰው ልጅ ክብርን፣ የሕግ የበላይነትንና የሀገር ሰላምን የማስጠበቅ ሓላፊነት ያላቸው በየደረጃው የሚገኙ ባለሥልጣናትና የሕግ አስከባሪ አካላት ጭምር እንደመሆኑ አሰቃቂ ጥቃት የፈጸሙት ተጠያቂዎች ለፍትሕ እንዲቀርቡ፤ ሌሎች ገዳማትና አድባራት ደኅንነታቸው እንዲጠበቅልን፤ ለተጎዱትም ተገቢው ድጋፍ እንዲደረግልን ዛሬም አበክረን እንጠይቃለን ።

በመጨረሻም ሕዝበ ክርስቲያንና መላው ኢትዮጵያውያን የጥቃት ሰለባ ከሆኑት ወገኖች ጋር በመንፈሳዊም ሆነ በሰብአዊ ድጋፍ አብራችሁ እንድትቆሙ ከአደራ ጭምር እያሳሰብን፤ በጽድቅ የሚፈርደው እግዚአብሔር አምላካችን ለተበደሉት ፍትሕን፣ ለቆሰሉት ፈውስን፣ በግፍ ሕይወታቸውን ለተነጠቁት ዕረፍተ ነፍስን፣ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ፍጹም ሰላምን ይስጥልን እያልን አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።

እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም፤ ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
1,730005
የብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) መልእክት
_____
ባረክናክሙ እምቤተ እግዚአብሔር። ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችሁ (መዝ 118፥26)

ከሁሉ አስቀድመን የ2018 ዓ.ም ተመራቂ ደቀመዛሙርት ሁላችሁም ከመላው የዩኒቨርሲቲያችን ማኅበረሰብና ቤታሰቦቻችሁ ጋር እንኳን ደስ አላችሁ።

ይህ የትምህርት ዘመናችሁን ስታጠናቅቁ የምናከብረው የምርቃት መርሐ ግብር የመማራችሁን ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ በእምነት፣ በትዕግሥት እና በብርታት ያለፋችሁበትን ጉዞ ነው። የተወደዳችሁ ተመራቂ ደቀ መዛሙርት በሁሉም ፈተናና ችግር ውስጥ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነበር፤ ዛሬም ወደዚህ የክብር ቀን አድርሷችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ።

በክርስትና ሃይማኖት ወደ አዲስ የሕይወት ምዕራፍ ሲገባ፣ እውነተኛ ስኬት በዲግሪ ወይም በስም ብቻ እንደማይለካ አስታውሱ። በፍቅር፣ በትሕትና፣ በታማኝነት እና በአገልግሎት የምታመጡት የሕይወት ለውጥ ከሁሉም የላቀ ነው። በፊታችሁ ያለው መንገድ የማይታወቅ ሊመስል ይችላል፤ ነገር ግን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጀመረው ቅዱሳን ሐዋርያት እና ሐዋርያውያን አበው የተከተሉት፣ አበው ቅዱሳን ያስቀጠሉት እስከ ምጽአተ ክርስቶስ የሚቀጥል የሕይወት መንገድ መሆኑን ላስታውሳችሁ እወዳለሁ።

“እኔ መንገድ እና እውነት፣ ሕይወትም ነኝ” (ዮሐ 14፥6) በማለት ያስተማረን አምላክ የጉዟችሁ መነሻና መድረሻ፣ የድካማችሁ ብርታት፣ የሃይማኖታችሁ ጽናት፣ ኃይልና ጉልበት መሆኑን እንድታስታውሱ አሳስባችኋለሁ። እርሱ ራሱ “እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ (28፥19) በማለት አብሮን እንደሚሠራ የገባውን ቃል ኪዳን እያሰባችሁ በእርሱ ያለውን ተስፋ፣ ጥንካሬ እና ዓላማ ዘወትር አስታውሱ። ያገኛችሁትን እውነትና ዕውቀት ለራሳችሁ ብቻ ሳይሆን ለምታገለግሉታና ለተላካችሁበት ማኅበረሰብ ጥቅም አድርጉት። በምትሄዱበት ሁሉ “እንደ እባብ ልባሞች እንደ ርግብም የዋሆች” (ማቴ10፥16) በመሆን የብርሃን እና የተስፋ ምሳሌ ሁኑ።

የአገልግሎት ጉዞ ከፍታና ዝቅታ፣ አድካሚና አሰልቺ፣ እንደመሆኑ መጠን ሊከተላችሁ ሳይሆን እንድትከተሉት የሚያባብላችሁ፣ እንድታሳምኑት ሳይሆን ምርኮኛ ሊያደርጋችሁ የሚፈልግ ዓለም ከፊታችሁ ይጠብቃችኋል። እናንተ የክርስቶስ ወንጌል መልእክተኞች በመሆናችሁ ከዓለም የተለዩ የሰማያዊው መንግሥተ እግዚአሔር አምባሳደሮች ናችሁ እንጂ የብልጭልጩና ታይቶ የሚጠፋው የዚህ ዓለም ምርኮኞችና ቅጥረኞች አይደላችሁም። በምትሔዱበት ሁሉ የላከቻችሁን የእናት ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት ጠብቃችሁ አስጠብቁ። በጥበብ ተመሩ። በፍቅርም አገልግሉ። ያገኛችሁት እውነትና ዕውቀት ለራሳችሁ ብቻ ሳይሆን ለሌሎች በረከት እንዲሆን በጥበብ አድርሱ። የምትጓዙበት መንገድ አስቸጋሪ ቢሆንም፣ መፈተናችሁ ከምትጠብቁት አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን ከማትጠብቁት፣ ይረዱናል፣ ይረዱናል ከምትሏቸውም በኩል ይሆናልና ተስፋ አትቁረጡ። ከክረምት ቀጥሎ በጋ፣ ከጨላማ በኋላ ብርሃን፣ ከመከራ ባሻገር ደስታ እንደሚመጣ የታወቀ ነው። በመልካም አገልጋዮች ዘንድም ከብዙ ድካም በኋላ ዘላለማዊ እረፍት እንዳለ እናምናለን።

መጠራታችሁንና መመረጣችሁን ታጸኑ ዘንድ ከፊት ይልቅ ትጉ (2ኛ ጴጥ 1፥10) እንዳለ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ እግዚአብሔር በእናንተ መታመን የጀመረውን መልካም ሥራ ይፈጽማልና በእምነት በፊታችሁ ያለውን ሩጫ ሩጡ። በእግዚአብሔር ታመኑ፣ በእርሱ የሚታመኑ ሁሉ በበጎ ጥበብ የተሞሉ ናቸው። ቤተክርስቲያናችን ዕውቀት ያላቸውን ብቻ ሳይሆን፣ ርኅራኄ፣ ታማኝነት እና ፍቅር ያላቸውን ሰዎች ትፈልጋለች። ስለዚህ በሕይወታችሁ ሁሉ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የአባትነት ብርሃን ይታይባችሁ። ለመራራው ዓለም ማጣፋጫ፣ ሥጋዊው ዓለም ላደከመቻቸው ብርታት፣ ለቆሰሉና ለታመሙ ሐኪም፣ ግራ ለገባቸው መፍትሔ ልትሆኑ ነቢዩ ዳዊት እንደተናገረው ዛሬ ከቅድስት ቤተክርስቲያን ለቅድስት ቤተክርስቲያን በቅድስት ቤተክርስቲያን መረቅናችሁ።
በየትምህርት መርሐግብራችሁ ላለፉት የትምህርት ዓመታት ያስተማረቻችሁ፣ ለዚህ መዐርግም ያበቃቻችሁ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከእናንት በሁሉም ዘርፍ ብዙ ትጠብቃለች፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በፊልጵስዩስ መልእክቱ የመማርንና የማገልግልን ምንነት አስረግጦ እንደነገረን “የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም ዐውቃለሁ መብዛትንም ዐውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” (ፊል 4፡1-13) እንዳለ በትምህርት ቆይታችሁ ዐውቀናል ስትሉ አለማወቅን አላወቅንም ስትሉ ጥበብን፣ በድካማችሁ ብርታትን ተምራችኋል፡፡ አሁን ደግሞ የበለጠው የኑሮና የሕይወት ትምህርት ቤት ከፊታችሁ አለ። በመኖርና በማገልግል የምትማሩበት፤ በቃል የሰማችሁትን በተግባር የምታዩበትና የምታሳዩበት፤ በጽሑፍ ያነበባችሁትን በአደባባይ የምትመሰክሩበት አዲሱና ቀጣዩን ትምህርት ቤት እንደጀመራችሁ ዕወቁ፡፡

በዚህ የሕይወትና አገልግሎት መስክ ችግር የምትፈቱ እንጂ ችግር የምታወሩ እንዳትሆኑ። ፈተናንን ምታሸንፉ እንጂ የፈተና ምክንያት ተደርጋችሁ እንዳትቆጠሩ። የሰውን ሸክም የምትሸከሙ እንጂ ሸክም እንዳትሆኑ። የጠበበውን የምታሰፉ፣ የተቆለፈውን የምትከፍቱ፣የተጣመመውን የምታቀኑ፣ የደፈረሰውን የምታጠሩ የጨለመውን የምታበሩ፣ አልጫውን የምታፍጡ እንድትሆኑ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ከአደራ ጋር ወደ ችግረኛው ዓለም ከዛሬ ጀምሮ ልካችኋለች፡፡ ታማኝ መልእክተኛ ለመሆን ያብቃችሁ።

ውድ ተመራቂ ደቀመዛሙርት!
ዛሬ ከታላቁ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በቅዱስ ፓትርያርኩና በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬ ስንመርቃችሁ ትምህርት በቃችሁ እያልን እንዳልሆነ ታውቃላችሁ። ይኽ የምረቃታሁ ዕለት በአንድ በኩል ለተቀደሰው አገልግሎት የጥሪ መጀመሪያ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የነገረ መለኮት ትምህርት ተምረው የማይጨርሱት እንደመሆኑ ወደ ሌላው የትምህርት መንገድ መሻገሪያችሁ እንደሆነ ልብ በሉ።

ከዚህ ተቋም የምትወጡት ዕውቀትን በአእምሮአችሁ ብቻ ሳይሆን፣ ጥሪን በልባችሁ ተሸክማችሁ ነው። እንደሚታወቀው ትምህርተ እግዚአብሔር (ቴዎሎጂ) የመጻሕፍት ንባብ ትምህርት ብቻ አይደለም። የእግዚአብሔርን እውነት፣ ፍቅር እና ለሰው ልጆች ያለውን ዓላማ የምንረዳበትና መንፈሳዊ ሕይወትን የምናዳበርበት፣ አእምሮን የምንገነባበት መንገድ ነው። ስለዚህ ወደ አገልግሎት፣ ስትሰማሩ ወይም ወደ ትምህርትና ሌላ ጥናት ስትገቡ፣ ዓለም የሚፈልገውን ብቻ የምትናገሩ ሳይሆን ዓለም እናንተ የምትናገሩትን የሚሰማ የቃሉ ታማኝ አገልጋዮች እንድትሆኑ ነው። ሕይወታችሁ ከቃላችሁ በላይ ይስበክ። በትሕትና፣ በቅንነት፣ በፍቅር እና በመንፈሳዊ ወኔ ተመላለሱ። እግዚአብሔር በጥበብ፣ በሰላም እና በበረከት ይምራችሁ።

አባ ፊልጶስ (ዶ/ር)
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣
የደበብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ
አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
ሰኔ 27፤2018 ዓ.ም
2,060008
Photo
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ልዩ ሥጦታ ተበረከተላቸው
___

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት እና የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ (ዶ/ር) በቅርቡ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን በከፍተኛ ማዕረግ ማጠናቀቃቸውን ተከትሎ ዛሬ ሰኔ 27 ቀን 2018 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲው ደቀ መዛሙርቱን በሚያስመርቅበት ወቅት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት እጅ ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ገበታው የወርቅ ቅብ የሆነ የቅዳሴ መጽሐፍ ተበርክቶላቸዋል።

በተጨማሪም ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የምሥራቅ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የኢኦተቤ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት የበላይ ሓላፊ በራሳቸው እንዲሁም በሚዲያው በኩል የተለያዩ ሥጦታዎችን ሠጥተዋል።

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት
2,080004
በመላው ዓለም፣ በደቡብ አፍሪካና በሳውዲ ዐረቢያ የሚኖሩ ዜጎቻችን ሰብዓዊ መብት እንዲከበር፣ የርኅራኄ ምሕረትና ፍትሕ እንዲያገኙ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ክትትል እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ጥሪውን በማቅረብ ለሰባት ቀናት ሲያካሂድ የሰነበተውን ቀኖናዊ ጉባኤ ዛሬ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም. በጸሎት አጠናቋል፡፡

“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ”

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ/ም
586003
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነችው ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ሲኖዶሳዊ በመሆኗ አበው ቅዱሳን በፍትሕ መንፈሳዊና በጉባኤ አድያም ዘአንጾኪያ “ወይኩን ሲኖዶስ ዘጳጳሳት ፪ተ ጊዜያተ በበዓመት - የጳጳሳት ጉባኤም በዓመት ሁለት ጊዜ ይሁን” ብለው በደነገጉት ቀኖና መሠረት፤ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚመራው፣ የሐዋርያት መንበር ወራሽ የሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤውን በኅብረተ መንፈስ ቅዱስ ከሚያዝያ 28 እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ አካሄዷል፡፡

ምልዓተ ጉባኤው ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለ ቤተ ክርስቲያን አንድነት፤ ስለ ሰው ልጅ ሁሉ ደኅንነትና ክብር፣ በአጠቃላይ ወቅታዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ሰፊ ውይይቶችን በማድረግ ዘመኑን የዋጁ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡ ከውሳኔዎቹም መካከል፡-

የቤተ ክርስቲያናችንን አንድነት መጠበቅና ማስጠበቅ የቅዱስ ሲኖዶስ ተግባር በመሆኑ ጥንታዊትና ሐዋርያዊት የሆነችውን ቤተ ክርስቲያን በአንድነቷና በሉዓላዊነቷ እንደተረከብናት ለወደፊቱም ሉዓላዊ ክብሯ ተጠብቆ እንድትቀጥል በምልዓተ ጉባኤው የተሠየመው በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራው “የሀገራዊ ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት” ኮሚቴ ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

ሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ በተረጋጋ መንገድ እንዲካሄድ፣ ለሀገር ሰላምና ለሕዝብ አንድነት በሚጠቅም ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምትጸልይ ሲሆን ምርጫው በሁሉም ወገን ለኢትዮጵውያን ዘላቂ ሰላምንና መረጋጋትን የሚያስገኝ ሆኖ እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንዖት ያሳስባል፡፡

ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የአርሲ ሀገረ ስብከትን በሊቀ ጵጵስና በቋሚነት እንዲመሩ፣ ሕዝቡን እንዲያጽናኑ እየደረሰ ያለውን ችግር ከቋሚ ሲኖዶስና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ከሚመራው የሰላም ኮሚቴ ጋር በመሆን የሚመለከተውን የመንግሥት አካል በማነጋገር ዘላቂ መፍትሔ እንዲያፈላልጉ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡

ከጥንት ጀምሮ “ቅዱስ ሲኖዶስ” በሚል ርእስ እየተዘጋጀ ይታተም የነበረው ታሪካዊ መጽሔት የቅዱስ ሲኖዶስ ቀኖናዊ ውሳኔዎችን በማካተት በቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት አስፈጻሚነት ሕትመቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

የቤተ ክርስቲያናችንን ደንቦች መመሪያዎች መርምሮ ማጽደቅ የቅዱስ ሲኖዶስ ሉዓላዊ ሥልጣን በመሆኑ፡-

የስብከተ ወንጌል ሐዋርያዊ ተልእኮ ማስፈጸሚያ ደንብ በብፁዕ አቡነ ማርቆስ ሰብሳቢነት

የአንድነት ገዳማት ኅብረት መተዳደሪያ ደንብ ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስና ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ባሉበት በድጋሚ እንዲታይና ሌሎቹም ለውሳኔ የቀረቡ ደንቦች በሊቃውንትና በሕግ ባለሙያዎች ታርመው ለጥቅምት 2019 ዓ/ም ምልዓተ ጉባኤ እንዲቀርቡ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል

የቀድሞው የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ “የቤተ ክርስቲያን ታሪክ በዓለም መድረክ”ና “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ” በሚሉ አርእስት አዘጋጅተው ያሳተሟቸው መጻሕፍትን የማሳተምና የማሰራጨት የባለቤትነት መብት ከሚያዝያ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ለዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እንዲሆን ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

ከተለያዩ አህጉረ ስብከት በቀረቡ ጥናቶችና የማጣራት ውጤቶች መሠረት፡-

የደቡብ ሱዳን ሀገረ ስብከት ከምሥራቅ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ጋር ተደርቦ በብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ሊቀ ጳጳስ እንዲመራ፤
ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል ሊቀ ጳጳስ የጋምቤላንና የቤንሻንጉል ጉምዝ አህጉረ ስብከትን ብቻ እንዲመሩ፤
ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ የጅማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጰስ የሰሜን ጎንደር ሀገረ ስብከትን እንደያዙ እንዲቀጥሉ፤
ብፁዕ አቡነ ኤፍሬም የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቄለም ወለጋ ሀገረ ስብከትን ደርበው በአባትነት እንዲመሩ፣
የኮንታ ዞን ሀገረ ስብከት እንዲሆን የቀረበው ጥያቄ የጸደቀ በመሆኑ ሀገረ ስብከቱ ራሱን ችሎ እንዲደራጅና በብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳስ እንዲመራ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፤
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የልማት ተግባራትን ምልዓተ ጉባኤው በከፍተኛ ደረጃ በማድነቅ፣ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክ/ ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ሲቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ በአባታዊ አመራር የፈጸሙት አስደናቂ የሥራ አፈጻጸም በጉልህ የሚታይ ለውጥ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የሚጠቅም፣ ሉዓላዊ ክብሯን የሚያስጠበቅ፣ ለሁሉም አበው ምሳሌነት ያለው በመሆኑ ምልዓተ ጉባኤው እጅግ ከፍ ባለ ክብር አመስግኗል፡፡

በዚህም መሠረት በብፁዕ ጠቅላይ ዋና ሥራ አስኪያጁ አባታዊ መሪነት እየተከናወኑ ያሉት ተግባራት ማለትም፡-

የቤተ ክርስቲያንን ቀደምት ሠነዶች በዲጂታል ቴክኖሎጅ እንዲደራጁ የተደረገበት ሥልት ተጠናክሮ እንዲቀጥል፤

ከ1970 ዓ/ም ጀምሮ በመጋዝን ተከማችተው የቆዩ በርካታ ልዩ ልዩ መጻሕፍትን የማሠራጨት ሂደት በተጀመረው መንገድ እንዲጠናቀቅ፤

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የኢንፎርሜሽንና ኮምኒኬሽን ተጠቃሚ እንድትሆን የተጀመረው ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ በሁሉም የቤተ ክርስቲያናችን መዋቅር በየደረጃው ተጠናክሮ ተግባራዊ እንዲሆን፤

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥር የተጀመሩ የሕንፃ ግንባታዎችና አጠቃላይ የልማት ሥራዎች በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ሁሉም አህጉረ ስብከትና ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦና ትብብር እንዲያደርጉ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጽንዖት ያሳስባል፡፡

በሰሜን አሜሪካ የሰሜን ካሊፎርኒያ፣ ኔቫዳና አሪዞና ሀገረ ስብከት ኆኅተ ሰማይ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስና ቅድስት አርሴማ ገዳም የመንፈሳዊ ኮሌጅ፣ የአብነት ት/ቤት ሥርዓተ ትምህርት የቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖና፣ ታሪክና ትውፊት በጠበቀ መልኩ ተጠናክሮ መዋቅራዊ ተጠሪነቱም በአግባቡ ተጠብቆ ሥራ ላይ እንዲውል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ያቀረበውን የ2019 ዓ/ም በጀት በማጽደቅ በተገቢው መንገድ ሥራ ላይ እንዲውል ምልዓተ ጉባኤው ወስኗል፡፡

በመጨረሻም ቅዱስ ሲኖዶስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በተነጋገረባቸው ጉዳዮች በትኩረት የተወያየው የቤተ ክርስቲያናችንን ሁለንተናዊ ዕድገትና ተቋማዊ ሕልውና ስለማስጠበቅ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ሀገራችንን ጨምሮ በመላው ዓለም እየታየ ያለው ግጭትና የሰላም መታጣት በእጅጉ አሳስቦታል፡፡

በመሆኑም ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሰላም፣ ስለ ሰው ልጆች ደኅንነት፣ በየቦታው በሃማኖታቸው ምክንያት መከራ የሚደርስባቸውን በየቦታው የሚገኙና ግጭት ባለባቸው ቦታዎች ያሉ ኦርቶዶክሳውያንን በማሰብ በመጪው የ2018 ዓ/ም ጾመ ሐዋርያት በመላው ዓለም ባሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት፣ አድባራትና አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎተ ምሕላ እንዲደርስ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
522005
ሰላም እንደምን ሰነበታችሁ ውድ የ2018 ዓ.ም ተመራቂ  ደቀመዛሙርት። ተመራቂዎችን የተመለከቱ መልእክቶች እንዲተላለፉበት በምርቃት ኮሚቴው የቴሌግራም ገጽ ተከፍቷል። በመሆኑም ተመራቂዎች  መልእክቶችን በቀጥታ ከአንድ ቋት ብቻ እንዲከታተሉ ተመራቂ ደቀ መዛሙርትን ብቻ Add በማድረግ ወይም ይህን Link https://t.me/htugc18  በመላክ   እንድትተባበሩን እናሳስባለን።

የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች ምርቃት ኮሚቴ
879003
፻፴፬ ኛው የቅዱስ ሲኖዶስ መደበኛ ምልአተ ጉባኤ ላይ በቅዱስነታቸው የተላለፈ አባታዊ መልእክት

ሚያዝያ ፳፳/፳፻፲፰ ዓ.ም

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ የግንቦት ርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የመክፈቻ አባታዊ መልእክት አስተላልፈዋል።
መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ ኣምላክ ኣሜን!
ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፤
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ
የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፤
ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ ኣባላት፣
በአጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የተገኛችሁ በሙሉ፦
ማሕየዊት በምትሆን ሞቱ ሰማያውያንና ምድራውያንን ያስታረቀ፣ በቅድስት ትንሣኤውም የሙታንን ሕይወት በተስፋ ያለመለመ ጌታችን፣ ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ እንኳን ለዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ አደረሰን አደረሳችሁ!
“እስመ ተዋለጠ እግዚአብሔር ዓለመ በክርስቶስ አናኅስዮ ኃጢአቶሙ ወኢነጺሮ ጌጋዮሙ፤ ወረሰየ ላዕሌነ ቃለ ሥምረቱ፤ ወወሀበነ መልእክተ ሣህሉ፤ እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና በደላቸውን አይቈጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ” (2ኛቆሮ. 5፥19)
የእግዚአብሔርም ልጅ፣ የሰውም ልጅ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ዓለም ሰው ሆኖ ሲገለጽ ግልጽ የሆነ ዓላማና ግብ እንደነበረው ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል፤ እርሱም በሰማይም፣ በምድርም ያሉትን በሙሉ ማስታረቅ፣ ማገናኘትና አንድ ማድረግ ነበረ፤
ጌታችን ይህንን ሲያደርግ ሰማያውያኑንና ምድራውያኑን የለያየውን ምክንያት በማስወገድ ነው፤ የመለያየቱ ምክንያት ክፉ ኅሊና አምጦ የወለደው በደልና እርሱን ተከትሎ የተከሠተው ኃጢኣት ነበረ፤ በኃጢኣት ምክንያት የገባው ሞት ደግሞ የቅጣቱ ማሳያ ፍርድ ነበረ።
የመጀመሪያዎቹ ሰዎች በፈጸሙት ስሕተት መነሻነት ምድርንና ምድራውያንን ለከባድ ቅጣትና መርገም የዳረገው ይህ መለያየት ለሰማያውያኑም ተርፎአል።
ምክንያቱም መለያየቱ በእግዚአብሔርና በሰው፣ በመላእክትና በሰው፣ በሰውና በሰው፣ በነፍስና በሥጋ ጭምር የጥል ግድግዳን ገንብቶ እስከ ክርስቶስ ዕለተ ስቅለት መዝለቁን በቅዱስ መጽሐፍ የምናውቀው ስለሆነ ማለት ነው።
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!

ቀዳማዊና ዘላለማዊ የሆነው ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰብእናችንን ተዋሕዶ በዚህ ዓለም የተገለጸው ሰማያውያንንና ምድራውያንን የለያየው የጥል ግድግዳን ለማፈራረስ ነው።
ለመለያየት ምክንያት የሆነችውን ኃጢኣት በሰውነቱ በመቅጣት የሕግን ትእዛዝ ከፈጸመ በኋላ የዕርቁን ተግባር በወሳኝ መልኩ አከናውኖታል።
በክርስቶስ ቤዛነት የሆነው ይህ ዕርቅ በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ የተወደደ ነበረና እሱ ራሱ በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር አስታረቀ።
ለዚህም ነው ተበዳይ እርሱ፣ ቤዛዊ መሥዋዕት ሆኖ የቀረበው እርሱ፣ ኣስታራቂ እርሱ፣ ታራቂ እርሱ ሆኖ የምናገኘው፤ ለእርሱ የሚሳነው ነገር የለምና ለእኛ ግር የሚል ቢመስልም ለእርሱ ቀላል ነበረ።
በዚህ የዕርቅ ተግባር ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሰውና ሰው፣ ነፍስና ሥጋ ታርቀው በይፋ ተገናኙ፤ በኅብረትና በአንድነትም መኖር ቻሉ፤ በቀኙ ለተሰቀለው ወንበዴ “ዛሬውኑ ከእኔ ጋር በገነት ትኖራለህ” የሚለው ቃለ ምሕረትና “አባት ሆይ፥ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ” የሚለው ቃለ አማኅፅኖ የዕርቁ፣ የግንኙነቱና የኣንድነቱ ማሳያ ኣስረጅ ናቸው።
ስቅለተ ክርስቶስ ነፍሶቻችን ወደ ግዞት ቤት ሳይሆን ወደ ገነት እንዲገቡ፣ የሚቀበላቸውም ራሱ እግዚአብሔር እንዲሆን ያስቻለ ታላቅ መለኮታዊ ፍጻሜ ነው።
እኛ “ክርስቶስ መድኃኒታችን ነው፤ አድኖናል” ብለን በፍጹም ልባችን አምነን የምንመሰክረው፣ እርሱም በመስቀል ላይ ውሎ “ሰላሜን ሰጠኋችሁ” በማለት በመስቀሉ ስላዳነን አጽናኝ መንፈስ ቅዱስንም ስለላከልን ነው።
ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት!
የድኅነታችንና የሰላማችን መሠረት የሆኑትን የክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ለዓለም ማኅበረሰብ የማብሰርና የማሥረጽ ተግባር የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ቍጥር አንድ ተልእኮ ነው፤
ነገረ ሞቱና ነገረ ትንሣኤው በአስተውሎት፣ በጥልቀትና በተመሥጦ ስናስተምር በውስጡ የምናገኘው የዕርቅ፣ የሰላምና የኣንድነት ምስጢር ነው፤
እንደ እውነቱ ከሆነ እኛ የክርስቶስ መልእክተኞች እንደ ቃሉ ራሳችንን ክደን በሚጠበቀው መጠን ተልእኮኣችንን መወጣት ብንችል ኖሮ፣ ኣሁን በዓለማችን የተፈጠረው መለያየትና ግጭት አይኖርም ነበር።
ችግሩን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ባንችልም በእጅጉ መቀነስና ዓቅሙን ማዳከም እንችል ነበር፤ ነገር ግን ተልእኮአችንን በአግባቡ አለመወጣት ኣንድ ነገር ሆኖ የዓለሙ መሣሪያ ሆነን መገኘታችን “በዕንቅርት ላይ…” ሆኖ ይስተዋላል።
ይሁንና አሁንም ሕዝቡን ወደ አንድነት፣ ወደ ፍቅር፣ ወደ ሰላም፣ ወደ ዘላቂ የጋራ ጥቅምና ወደ ፈሪሀ እግዚአብሔር ማምጣት የጉባኤያችን ዐቢይ ተግባር ሊሆን ይገባል፤ እነዚህ ካሉ የምናጣውም ሆነ የሚያመልጠን የለምና ነው፤
ሀገርን በኀላፊነት ተረክባችሁ በላዕላዊ፣ በማእከላዊና በታሕታዊ መዋቅር የምትገኙ፣ እንደዚሁም አማራጭ ሐሳብ አለን ብላችሁ የምትንቀሳቀሱ ልሂቃነ ሀገር ፣ ሁላችሁም እግዚአብሔርን ከሚያውቅ፣ ከሚያመልክና ከሚፈራ ሕዝብ የተገኛችሁ ናችሁና በልባችሁ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ድምፁንም ስሙ፤ የእርሱ ገንዘብ በሆኑ ፍጡራንም አትጨክኑ፤ ሰውን መያዝ የሚቻለው ኅሊናን በመርታት እንጂ በሌላ አይደለምና፣
የሕዝቡን ፍላጎትና የልብ ትርታ በሚገባ አዳምጡ፤ ሕዝቡ የሚፈልገው በአንድነትና በእኩልነት መኖር፣ በሰላም ወጥቶ መግባት፣ ፍትሕን ማስፈን፣ ለኑሮው የሚበቃ ምጣኔ ሀብትን ማግኘት፣ የእምነት ነፃነትና እኩልነት መረጋገጥ የመሳሰሉት ናቸው።
ሕዝቡ እነዚህ ከተሟሉለት ተደመጠ ማለት ነው፤ ከተደመጠ ደግሞ እርሱም በበኩሉ ያደምጣል፤ ይከተላልም።
ስለሆነም ለሁሉም ልጆቻችንና ወገኖቻችን የምናስተላልፈው ወቅታዊ ጥሪ ሁሉንም ችግሮቻችንን በሰላም ብቻ ለመፍታት ተባበሩ የሚል ነው፤ ከዚህ ውጭ የሚደረገው አማራጭ ሁሉ ለዘላቂ ሰላማችን አይበጅም እንላለን።
በመጨረሻም፦
በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት ከበዓለ ትንሣኤ በኋላ በሃያ አምስተኛው ቀን የሚካሄደው ዓመታዊው የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በዛሬው ዕለት የተጀመረ መሆኑን ለሕዝበ ክርስቲያኑና ለመላው ኢትዮጵያውያን እናበሥራለን!!!
እግዚአብሔር ጉባኤያችንን ይባርክ!
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር፤
አሜን!!!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፤
ሚያዝያ ፳፰ ቀን ፳፻፲፰ዓ.ም
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

ዘገባው የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መገናኛ ብዙኃን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት ነው።
1,420000

Showing 30 of 34 posts

رتبه‌بندی

ورود لازم است

Frequently Asked Questions

کانال تلگرام የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት-Holy Trinity University PR درباره چیست؟+

የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት-Holy Trinity University PR (@holytrinitypr) یک کانال تلگرام در دسته اخبار کسب‌وکار در tgdio است. این پروفایل رتبه، امتیاز، نظرات و پست‌های تازه را نشان می‌دهد تا قبل از عضویت تصمیم بگیرید. در حال حاضر حدود ۲٬۳۷۶ مشترک در tgdio دارد.

چطور به የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት-Holy Trinity University PR (@holytrinitypr) در تلگرام بپیوندم؟+

پروفایل کانال را در tgdio باز کنید، سپس با دکمه Join / Open in Telegram به @holytrinitypr بروید و رایگان عضو شوید.

آیا የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት-Holy Trinity University PR کانال خوبی در اخبار کسب‌وکار است؟+

در tgdio می‌توانید قبل از عضویت امتیاز، نظرات، رتبه و پست‌های የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት-Holy Trinity University PR را بررسی کنید. در حال حاضر حدود ۲٬۳۷۶ مشترک در tgdio دارد. آن را با کانال‌های مشابه اخبار کسب‌وکار مقایسه کنید.

آمار و پست‌های የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት-Holy Trinity University PR را کجا ببینم؟+

در tgdio صفحه @holytrinitypr را برای آمار اعضا، رتبه، امتیاز و پست‌ها باز کنید. لینک Stats نمودار رشد را نشان می‌دهد.